የትኛው ጨዋታ ከባድ ይሆናል? የቡርኪናፋሶ ወይስ የናይጄሪያ
አደራ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ፖለቲካውን በዚህ ሰሞን ገታ ያድርግልን!!!!!!
ኤፍሬም እሸቴ
ዛሬ ሐሙስ ረዥም ቀን እንደሚሆንብን እገምታለኹ። መች ነግቶ የኢትዮጵያንና የቡርኪናፋሶን ጨዋታ ባየን የሚለው የብዝዎቻችን ሐሳብ ነው። ብሔራዊ ቡድናችን ከዛምቢያ ጋር ባሳየው “ደረጃውን የጠበቀ እግር ኳስ” (World Class football”) ምክንያት የዓለምን ዓይን ስቧል። ስለዚህ የሚጠበቅበትም እንደዚያው ደረጃው ከፍ ብሏል።