ባንኮች የስምንት ወራት ሰነድ ግዥ ውዝፍ መክፈል ጀምሩ ተባሉ
በአስራት ሥዩም
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ቀደም ሲል በባንኮች ላይ ተጥሎ የነበረውን የብድር ገደብ በማንሳት የግምጃ ቤት ሰነድ ግዢ መመሪያ ካወጣ በኋላ፣ ባንኮቹ ካለፈው ሐምሌ 2002 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ የካቲት 2003 ዓ.ም. ድረስ ለሰጡት ብድር 27 በመቶ ውዝፍ የግምጃ ቤት ሰነድ ግዢ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ እንዲከፍሉ ታዘዋል፡፡