በቃ! ገዬ! በስ! አሎኒ! ጊደስ!
በስዊድን የኢትዮጵያውያን የሰልፍ ውሎ
Ethiopia Zare (ቅዳሜ ሚያዝያ 1 ቀን 2003 ዓ.ም April 9, 2011)፦ ትናንት ዓርብ መጋቢት 30 ቀን 2003 ዓ.ም. ትንሽ ትንሽ፣ ብን ብን ከሚለው ዝናብ በስተቀር ይሄን ያህል ብርድ አልነበረም። የስዊድን ክረምት (ዊንተር) ከመቼውም በበለጠ ሁኔታ እንኳን ለስደተኛው ለዜጋውም አልገፋ ብሎ በረዶው በአንዳንድ ከተሞች ከመሬቱ አልላቀቅ ብሎ ሙጭጭ ያለበት ዓመት ነው – የአውሮጳውያኑ 2011። የአየሩ ፀባይ አፈር ሲሉት ውሃ እንደሆነ የሚያውቀው ኢትዮጵያዊ ግን የክረምት ልብሱን አልወጠም። በሻርፕ ተጠቅሏል፤ ኮፍያውንም አልጣለም።