ርዕሰ አንቀጽ፡ በጅማ ፕሮቴስታንቶች ላይ የተፈፀመውን የአክራሪዎች ጥቃት ልንቃወም የሚገባበት ምክንያት …
(ደጀ ሰላም፤ ማርች 9/2011)፦ በጅማ አካባቢ ባሉ ሥፍራዎች “በጥቂት አክራሪ ሙስሊሞች” የተፈፀመውን ጥቃት በተመለከተ የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን የዘገቡትን ዘገባ እኛም በድጋሚ ትኩረት ሰጥተን ማስተናገዳችን ይታወቃል። እናውቃለን ፕሮቴስታንቶቹ የእኛኑ አማኞች ከርትዕት እምነታቸው ለማፈናቀል እንደሚጥሩ። እናውቃለን አብዛኞቹ ዛሬ “ፕሮቴስታንት ነን” ያሉት ወገኖች በእኛው ቤተ ክርስቲያን በ40 እና በ80 ቀናቸው የተጠመቁ እንደነበሩ። እናውቃለን ቤተ ክርስቲያናችንን በመናቅ እንደሚናገሩ። እናውቃለን ከዚህ በፊት በኦርቶዶክሳውያን ክርስቶያኖች ላይ ያ ሁሉ ጭፍጨፋ ሲፈፀም ድምጻቸውን እንዳላሰሙ። ነገር ግን አሁን የጥቃቱ ዒላማ እነርሱ ስለሆኑ ልንደሰት፣ ዝም ልንል፣ “ይበላቸው” ልንል አንችልም። ክርስትናችን አይፈቅድልንም። ይህ አደጋ የደረሰው በክርስቲያኖችም ላይ ሆነ በሌሎች እምነት ተከታዮች ላይ ድርጊቱን እናወግዝ ዘንድ እምነታችን ግድ ሊለን ይገባል። ይህንን የፈፀሙት ፕሮቴስታንቶቹ፣ ተጎጂዎቹ ሙስሊሞቹ ቢሆኑ ኖሮ ተጎጂዎቹን ሙስሊም ወንድሞቻችንን ደግፈን ወንጀሉን የፈፀሙትን እንቃወማቸው ነበር። ጥያቄው “ማን ነው የተጎዳው?” ሳይሆን “ማንም ይሁን ማን፣ እንዴት ይጎዳል?” ነው። አመክንዮዋችንን በሚከተለው ታዋቂ ጥቅስ እናጠቃለው።
(Read More ወደሚቀጥለው ገጽ ይዞራል . . . . .)