የጥፋት ራዕይ፤ የክህደት ሌጋሲ

ፍአ

ራዕይም ይባል ሌጋሲ፤ ህልምም ይባል ምኞት አንድ ነገር እውነት ነው። ሰውየው፤ ከተጀመረ ጀምሮ በሰላም ኑሮ እንቅልፍ አግኝቶ ስለማያውቅ ህልም አለመ፤ ራዕይም ነበረው፤ አስቦና መዝኖ ሠራ ለማለት አይቻልም። ከፊቱ ነገ አልነበረችም። ሊባል የሚቻለው፤ የነበረው የጥፋት፤ የማፍረስ፤ የመበተን፤ የክህደት ቅዠት ብቻ ነው።