የአበበ ገላው ጉዳይ
ክንፉ አሰፋ
የአቶ መለስ ዜናዊ ዜና እረፍት በተሰማ ማግስት አንድ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵአዊ ከአውሮፓ ለአበበ ገላው ስልክ ይደውልለታል። ግለሰቡ ደጋግሞ ሲደውል የአበበ የእጅ ስልክ ጠፍቶ ስለነበር ሶስት ተከታታይ የድምጽ መልእክቶችን ትቶ ነበር። “አበበ እባክህን ባስቸኳይ መልሰህ ደውልልኝ። አንተን በተመለከት ከአገርቤት የመጣ መረጃ አለ።እባክህን መልሰህ በዚህ ቁጥር አስቸኳይ ደውልልኝ።” ይላል መልእክቱ። ደዋዩ ከልብ እንደተጨነቀ ከድምጹ መረዳት ይቻላል።