የመዳኛ ወቅትና፤ የዕረቀ ሰላም ጊዜ

ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ)

የረፖርተር ድረገፅ ሲዘግብ

“በጎሳ ላይ የተመሰረተ ግጭት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መሃል በመጸዳጃ ቤቶች፤ በቤተመጻህፍትና በመኝታ ቤት ግድግዳ ላይ፤የተጻፉ አስፀያፊ ክብረነክ ጸሁፎች ከስድስት በላይ የሆኑ ተማሪዎችን ለከፍተኛ የመቁሰል አደጋ ተጠቂ ዳርጓቸዋል። በርካታዎችንም ለእስር አብቅቷል። ለላለፉት አሰርት ዓመታት፤በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መሃል ግጭቶችን ሲያስነሱ ከርመዋል። …