“አንድ ክርስቶስ!” “አንድ ሲኖዶስ!” “አንድ መንጋ!
(ወልደ አረጋዊ፤ በተለይ ለደጀ ሰላም እንደጻፉት/ PDF)፦ ሕይወት ጣፋጭም መራራም ጽዋዋን ደጋግማ ትግታለች፡፡ ዛሬ ረቡዕ ሰው፣ ብሎም ኢትዮጵያዊ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታይ በመሆኔ ብቻ እጅግ መራራውን የሕይወት መርዶ ተጎንጭቻለሁ፡፡ ዛሬ በቤተ ክርስቲያኔና በምዕመኑ ላይ በግፍና በማን አለብኝነት ስለተዘጋብን
“የሰላም በር” መርዶ ሬት ሬት እያለኝ ሰምቸዋለሁ፡፡
“የሰላም በር” መርዶ ሬት ሬት እያለኝ ሰምቸዋለሁ፡፡
አባቶቻችን ፈረዱብን! እንዲያ ከአጽናፍ እስከ አጽናፍ ያስተጋባውን የመንጋው የተማኅጽኖ ጥሪ አልገደዳቸውም ነበር እና “ቅድሚያ ለምርጫ” ማለትን ወደዱ፡፡ እጅግ መራራ ነው፡፡ ይህን መስማትም ሆነ ማሰብ እጅግ ይመራል፡፡ በመለያየት ውስጥም መኖር ከሁሉም በላይ አብዝቶ ይመራል፡፡ አባቶቻችን ግን በእኛ በክርስቶስ የአደራ
ልጆቻቸው በምንሆን ላይ እጅግ አብዝቶ በሚመረው “የመለያየት ክርስትና” ውስጥ እንድንኖር ዛሬ በድጋሚ ፈረዱብን፡፡ አባቶቻችን አንድ እንዳንሆን በድጋሚ
ፈረዱብን!

ዘማሪው እንዳለው “ሰዎች ፈረዱብኝ አንተ ግን አዳንከኝ” ነውና ታሪካችን ከዛሬ ፳ ዓመታት በፊት የተገነባው የመለያየት ግድግዳ ዛሬም ተጠናክሮ እንዲቀጥል
ሰዎች ቢፈርዱብንም እግዚአብሔር ግን እውነተኛ አባትና የእኛ የልጆቹ መቅበዝበዝና ለክፉው ተላልፈን መሰጠታችን በእውነት የሚገደው
እረኛችን ነውና በእውነት ዝም አይልም፡፡ መንጋውን ከመቅበዝበዝ ያድናል ይሰበስበናልም፡፡ መጽሐፍ እንዳለው እርሱ እውነተኛ የበጎች ጠባቂ ነው!

“ክርስቲያን ተስፋ አይቆርጥም!” ይላል ያገሬ ሰው፡፡ እነሆ እኛም ኢትዮጵያዊ ክርስቲያኖች
ነን እና መቼም ቢሆን በክርስቶስ ተስፋ አንቆርጥም፡፡ እንግዲህ ለአለፉት ሦስት ዓመታት በተለየም ከብፁዕ ወቅዱስ
አቡነ ጳውሎስ እረፍት በኋላ በመላው ዓለም የምንገኝ የቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆች “ቅድሚያ ለዕርቅ” በሚል ዐቢይ ዓላማ ሥር ተሰባስበን አባቶቻችንን ስንማፀንና ስናግባባ ከርመናል፡፡ ይህ መንገድ ዛሬ
ረቡዕ ጥር ፰ ፳፼፭ በይፋ እንደተዘጋና “ቅድሚያ ለምርጫ” የሚለው ሐሳብ እንዳሸነፈ መርዶው ደርሶናል፡፡ ስለዚህ በአባቶቻችን የተዘጋውን የአንድነት በር ተስፋ በመቁረጥ እንቀበል ወይስ እኛም እንደቀደሙት
ክርስቲያኖች “ክርስቲያን ተስፋ አይቆርጥም!” እንበል?

እኔ “ክርስቲያን ተስፋ አይቆርጥም!” ከሚሉት ወገን ነኝ። ምክንያቱም በክርስቶስ የማይቻል ነገር እንደሌለ በተረዳ ነገር አውቄለሁና፡፡
ስለዚህ እኛ ክርስቲያኖች መቼም ቢሆን ስለ ሰላም፣ ስለ ፍቅርና፣ ስለ አንድነታችን ተስፋ አንቆርጥምና ምን እናድርግ? ወደሚለው
መሠረታዊና አግባብነት ያለው ጥያቄ
መሻገር ያለብን ይመስለኛል፡፡ ስለዚህ በእኔ በኩል ለመነሻ ይሆን ዘንድ የሚከተሉትን ሐሳቦች እነሆ፦

፩ኛ. የሰላምና የአንድነት ግብረ-ኃይል!
የአባቶቻችን መለያየት በተለይም “ውግዘቱ” እጅግ ሸክሙ የከበደውና ለያይቶን የሚገኘው በስደት ላይ በምንገኝው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ላይ መሆኑ እሙን ነው፡፡ ምክንያቱም የተወጋገዙቱ በጋራ የሚገኙት
ሀገር ቤት ሳይሆን እዚህ በውጭው ዓለም ነውና፡፡ ስለዚህ የችግሩ ግንባር ቀደም ገፈት ቀማሾች የሆን እኛ በምንኖርባቸው ከተሞች /ስቴቶች/ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በየቤተ ክርስቲያኑ አንዳንድ
ምዕመን በመወከል የጋራ የሰላም ኮሚቴ በማቋቋም ምዕመኑ በአንድነት እግዚአብሔርን የሚያመልክበት፣ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት የሚጠብቅበት፣ወደፊትም ሊሰሩ ስለሚገባቸው
ዐበይት ተግባራት የሚመክርበትና
ከሁሉም በላይ አንድነቱንና ሕብረቱን የሚያፀናበት መድረክ መፍጠር አለበት።

፪ኛ. “አንድ ክርስቶስ!”፣ “አንድ ሲኖዶስ!”፣ “አንድ መንጋ!”
በዚህ የሰላም ኮሚቴ አማካኝነት እዚህ
በስደት ያለው ምዕመን የአንድነትና የሰላም መንፈስ ወደ አገር ቤት የሚደርስበትንና እዛም ያለው ምዕመን ለቤተ ክርስቲያን ሰላምና ለአንድነቱ ተግቶ የሚታገልበትን
ሁኔታ ማመቻቸት ይገባል፡፡ ምክንያቱም በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እየሰማን ያለነው የሌላውን
45 ሚሊዮን ምእመን
መፈክሮች ነው፡፡ ይህ ደግሞ በስደት የምንገኘውን የቤተ ክርስቲያኒቱን ልጆች እንደ ውጭው ሲኖዶስ አባቶች ከአገር ቤቱ ክርስትና ለመለየት የተጠነሰሰልን የእብደት መንገድ ነው፡፡ ስለዚህ
ጥሪያችንም ሆነ መዝሙራችን አንድ ነው፡፡ይኸውም “አንድ ክርስቶስ!” “አንድ ሲኖዶስ!”“አንድ መንጋ!”

እናንተም አክሉበት!!!
ቸር ወሬ ያሰማን ብያለኹ!!! አሜን