ጧሪ ያጡ እናቶችን የቤት ባለቤት ያደረጉት የመቀሌ ባለሀብት

ሓጂ ዓብደላ ሓሰን በመቀሌ ከተማ የህንጻ መሳሪያዎች ነጋዴ ናቸው፡፡
እኚህ ግለሰብ ምንም ጧሪ ቤተሰብ ለሌላቸው 12 የመቀሌ ነዋሪ እናቶች ለያንዳንዳቸው መኖርያ ቤት ኣሰርተው ኣስረክበዋል፡፡ እያንዳንዱ ቤትም የራሱ መብራትና የውሃ ቆጣሪ፤ የገላ መታጠብያ፤ሽንት ቤት እና ኩሽና ቤት አለው፡፡

ሓጂ ዓብደላ ከዚህም በተጨማሪ መቀሌ በተለምዶ ቀበሌ 03 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚኖሩትን የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች እንዳይቸገሩ በማሰብ መስጊድ ኣሰርተውላቸዋል፡፡ እንዲሁም በመስጊድ ቅጥር ግቢ ማህበረሰቡ የሚጠቀምበት የውሃ ጉድጓድና ለመስጊድ የአስተዳደር ስራ የሚያገለግሉ ተጨማሪ ክፍሎችን ሰርተዋል፡፡
“ይህንን የማደርገው የኣባቴን ኣደራ ለመጠበቅ ነው ፤ልጆቼም የኔን ፈር ይከተላሉ ብዬ ኣምናለሁኝ” ይላሉ ሓጂ ዓብደላ፡፡

ላለፉት 40 ኣመታት የቆየውን የአባታቸውንም …