ፀረ ሙስና ኮሚሽን ትላልቅ ፕሮጀክቶችን ለመመርመር ከብሔራዊ ደኅንነት ጋር የተጣመረ ግብረ ኃይል እያቋቋመ ነው

በውድነህ ዘነበ

የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ትላልቅ የመንግሥት ፕሮጀክቶችን ለመመርመር የያዘውን ዕቅድ ለማሳካት፣ ከብሔራዊ ደኅንነት ኤጀንሲ ጋር በመቀናጀት ሥራውን የሚያካሂድ ግብረ ኃይል እያደራጀ መሆኑን ምንጮች ገለጹ፡፡