በጋምቤላ ክልል የወባ ወረርሽኝ ተከስቷል
– አሥር ሰዎች መሞታቸው ይነገራል
– የክልሉ ፕሬዚዳንት የሞተ ሰው የለም ብለዋል
በጋምቤላ ክልል አኝዋ ዞን በአቦህ ወረዳ በተከሰተ የወባ ወረርሽኝ በሁለት ቀናት ውስጥ አሥር ነዋሪዎች መሞታቸውንና በመቶዎች የሚቆጠሩ በአስቸኳይ የሕክምና ዕርዳታ ላይ እንደሚገኙ የአካባቢው ምንጮች ቢገልጹም፣ የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ኡመድ ኦቦንግ የሞተ ሰው የለም ብለዋል፡፡