የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ ዋና መምርያ ስድስት ኃላፊዎች በሙስና ተጠርጥረው ተከሰሱ

–    አራት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር አልዋሉም

በታምሩ ጽጌ

የተሰጣቸውን ሥልጣን ያላግባብ በመጠቀምና በመመሳጠር ለመንግሥት ገቢ መሆን የሚገባውን ከ1.7 ሚሊዮን ብር በላይ ለግል ጥቅማቸው አውለዋል በሚል በተጠረጠሩ ስድስት የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ መምርያ ኃላፊዎች ላይ፣ የፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ክስ መመሥረቱን ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡