የኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤት ቦርድ ኃላፊነቱን እንዲለቅ የቀረበው ጥያቄ እያወዛገበ ነው

በዳዊት ታዬ

የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤትን በቦርድ አባልነት በማገልገል ላይ የሚገኙት አቶ ሸዋዬ ገብሩ፣ እርሳቸው አባል የሆኑበትና  በአመራር ላይ ያለው ቦርድ ኃላፊነቱን መልቀቅ አለበት ብለው ለቦርዱ ያቀረቡት ደብዳቤ ውዝግብ መፍጠሩ ተገለጸ፡፡