ሰለሱሰ አምጪ መድሃኒቶች፤ እጽዋትና ተመሳሳይ ከሚካሎች ጎጂነት ወርቁ አበበ
በዚህ በአሚሪካ ከምኖርባት ትንሽ ከተማ ወጣ በማለት ብዙ ኢትዮጵያዊያን ወደሚኖሩባቸዉ ትላልቅ ከተማዎች ብቅ ባልኩ ቁጥር በርከት ያሉ ኢትዮጵያዊያን ሲጋራ ሲያጨሱና የአልኮል መጠጥ በገፍ ሲጠጡ ተመልክቻለሁ። ከዘመድና ከጋደኛም ጋር ምን አዲስ ወሪ አንዳለ ጨዋታ ሲጀመር፤ በወሪ መሃል አንዳንድ የአገራችን ስዎች በሱሰ አምጪ መድሃኒቶች፤ እጽዋትና ተመሳሳይ ከሚካሎች አንደተነካኩ ብዙ ጊዚ ሰምቻለሁ። ከትንሸዋ ከተማዮ ሳልወጣም፤ በተለያዩ የዚና ማሰራጭዎች አማካኝነት ኢትዮጵያዊያን አልፎ አልፎ ከጫት ጋር በተያያዙ የወንጀል ድርጊቶች ዓንደተስማሩ ለመገንዘብ ችያለሁ። በአኍኑ ወቅት ሱሰ አምጪ በሆኑ ነግሮች መለከፍ የኢትዮጵያዊያን ችግር ብቻ ሳይሆን የአልም አጠቃላይ ችግር ዓንደሆነ በስፋት ይነገራል፡ በተለይም ወጣቱን ትውልድ አስመንክቶ። ኢትዮጵያዊያንን በተመለከተ ስለዚህ ችግር የምሰማውና የማነበው ስላሳሰበኝና አዝማሚያውም ሰላላማረኝ፤ የሚመለከታቸውን ለማሳሰብ ያህል ይህንን አጭር ጽሁፍ ብዙዎቻችን በይበልጥ በምናውቀው ቃንቃ ለመጻፍ ተነሳሁ። አንዳንድ ቲኪኒካዊ የሆኑ ጉዳዮችን በብቃት ለመግልጽ አስቸጋሪ ቢሆንብኝም፤ አንባቢያን የጽሁፈን አጠቃላይ መልዓክት ይረዳሉ ብዮ ተስፋ አደርጋልሁ።
ለመሆኑ “ሱሰ” ሲባል ምን ማለት ነዉ? ባጭሩ ሱሰ አምጪ የተባለው ነገር ተደጋግሞ ዓንዲወሰድ የሚገፋፋ መጥፎ ልምድ ወይም ሁኒታ ማለት ነው። ዓንደሚወሰደው ነገር አይነትና ዓንደአወሳሰዱ ሁኒታ ዓንደዚሁም ዓንደወሳጁ የአዓምሮና በአካል አቅም የሱሱ አይነት ወይም ደረጃ ሊለያይ ይችላል። ለምሳሊ ያህል የሱሱ ሁኒታ ከፍተኛ ከሆነ፤ ሱሰኛው ለሱሰ አምጪው ነገር የአምሮም ሆነ የአካል ተገዥ ሊሆን ይችላል። በዚህን ጊዚ ሱሰኛው ፍላጎቱን ለማማላት ብዙ የማይጠበቁ ነገሮችን ለማድረግ ይገደዳል። በድርጊቱም ዓራሰን ብቻ ሳይሆን ሊሎችንም ሊጎዳ ይችላል።
በሱሰ ለመያዝ ዋና መነሻ ተብሎ የታመነው፤ ሱሰ አምጪው ነገር ከተወሰደ በሃላ በአዓምሮ ላይ በቅድሚያ የሚፈጥረው “የደስታ”፤ የዓርካታንና “የድል” መንፈሰ ነው። ይህ የአዓምሮ ሁኒታ ሱሰ አምጪው ነገር በማከታተል ዓንዲወሰድ የገፋፋል። በዚህ ብቻ ሳያበቃ የሚወሰደው ነገር ከጊዚ ወደ ጊዚ መጠኑን ዓየጨመረ ዓንዲወሰድ የሚያሰገድድ ሁኒታም ይፈጠራል። ሱሰኛው በዚህ ከቀጠለ የሚወሰደው መድሀኒት፤ አጽ ወይም ሊላ ተመሳሳይ ኪሚካል በሰዉነቱ ውሰጥ ረዘም ላለ ጊዚ በመቆየት በአካል ላይ አይነተኛ ለውጥ በማምጣት በመጨረሻ ሱሰ አምጪው ነገር ዓንደሚፈለገው ካልተወሰደ ሰዉነት በትክክል ለመሰራት ይሳነዋል። ሰለዚህ ይህንን ተደራቢ ችግር ለመቃቃም ሱሰኛው የለመደዉን ነገር ላለማቃረጥ አሰፋላጊውን ሁሉ ያደርጋል። ከላይ የተሰጠው ምሳሊ ከፍተኛ ለሆነ የሱሰ አይነት/ደረጃ ሲሆን፤መለሰተኛ የሆኑ የሱስ ጸባዮችም የሚታዩባቸው ብዙ ሁናታዎች አሉ።
በብዙ አካባቢዎች ሱሰ ሊያመጡ የሚችሉ በርካታ ነገሮች ሲኖሩ፡ በሰፋት ከታወቁት መካከል ጥቂቶቹ ቅጥሎ የተዘዘሩት ናቸው።
ማርዋና፡- ይህ ከአጽ የሚገኝ ሱሰ አምጪ የሆነ ነገር ነው። ካናቢስ በመባልም የጠራል። የማርዋና የተላያዩ ዝግጅቶች ሲኖሩ፤ በብዙዎች ዘንድ የታወቅዉ “ሀሽሽ” ዓየተባለ የሚጠራው ነው። ማርዋና የአዓምሮን ቦታና ጊዚን የማገናዘብ ችሎታንና የቅርብ ጊዚን ድርጊቶች የማሰታወስ ሃይል ይቀንሳል። በአንዳንድ ተጠቃሚዎች ላይ መደናገጥን፤ ጥርጣሪንና ቅዥትን ያመጣል። ብዙውን ጊዚ ማርዋና በማጫሰ የሚወሰድ ነው። ሱሰ ከማምጣት ባሻገር ማርዋና ሳንባን፤ ልብንና የርቢ አካላትን ሊጎዳ ይሚችል ነው።
ኮኪን፦ የዚህ ሱሰ አምጪ ነገር ምንጩ ዓንደገና ዓጽ ነው። ከማርዋና ጋር ሲወዳደር ኮኪን ከፍ ያለ ሱሰ የሚያመጣና በይበልጥም የሚጎዳ ነው። መረበሸን፤ መጠራጠርን፤ መቃዠትን፤ ፋታ ማጣትንና ቁጡኝነትን ያመጣል። በተጨማሪም ኮኪን የልብ መታወክን፤ የደም ብዛትን፤የሆድ ህመምን የፈጥራል። ኮኪን በተለያዩ መንግዶች የሚዘጋጅና የሚወሰድ ነው።
ሂሮይን፦ ይህ ኪሚካል በከፊል አመጣጡ ከዓጽ ነው። ሂሮይን ከባድ ሱስ ከሚያመጡ ነገሮች በካከል አንዱ ነው። ሲወሰድ ከሚያመጣቸው የጢንነት ቀዉሶች መካከል መፍዘዝን/መደንዘዝን፤ መምታታትን፤ ማቅለሸንሸን፤ የሆድ ድርቀትን፤ የመተንፈሰ ጭንቀትንና ዝግተኝትን ይፈጥራል። ሱሰኞች ሂሮይንን የሚወስዱት በመርፊ መልክ ነው።
የአልኮል መጠጥ፦ ይህ ሱሰ አምጪ ነገር ለመጀምሪያ ጊዚ ወይም በመጠኑ ሲወሰድ የሚያነቃቃና አዝናኚ ሲሆን፤ መጠጣቱ ግን ሲቀጥል አደንዛዥ ብሎም ሰውነትን የመቆጣጠር ችሎታን የሚያሳጣ ይሆናል። ረዘም ላለ ጊዚ በብዛት ሲወሰድ የጉበት በሽታን፤ የልብ በሽታን፤ የደም ብዛትን፤ የዐዓምሮና የነርቭ ህመምን ዓንደዚሁም ሊሎች ችግሮችን ያሰከትላል። በተነይ የአልኮል ተግዢ የሆነ ሰው ብዙ ችግሮች የሚታዩበት ነው። ከችግሮቹ መካከል ጠጪው አልኮን በማይወሰድበት ወቅት ከሞላ ጎደል ሁሉንም ሰውነቱን በመነካካት የሚታዩ ዓንደ ቅዥት፤ ትኩረት ማጣትን፤ የምግብ ፍላጎት መቀነስን፤ መንቀጥቅጥን፤ የልብ ትርታና የደም ብዛት መጨመርን የመሳሰሉ ህመሞች ይንጸባርቃሉ።
ጫት፦ ጫት በተለያዩ ህገ ወጥ በሆኑ መንገዶች ዓዚህ አሚሪካ ዓንደሚገባ ብዙ ጊዚ ተገልጻል። ለሚፈለገው አገልግሎት ጫት ብዙውን ጊዚ ቅጠሉን በማላመጥ ነው የሚወሰደው። ጫት ለአዓምሮ ጊዚያዊ ንቃትን የሚሰጥ ነው፤ ስለሆነም ብዙውን ጊዚ የሚወሰደዉ ለዚሁ ሲባል ነው። ጫት ለረጅም ጊዚ በተልይም በብዛት ሲወሰድ በቀላሉ ተናዳጅነትን፤ መሸበርን፤ ቅዠትን፤ መንቅዥቅዥን፤ መደበርን፤ በፍጥነት ተለዋዋጭ መሆንንና ዓንቅልፍ ማጣትን ያመጣል። በአንጎል ላይ ከሚያመጣው ችግር በላይ ጫት የደም ብዛትን ይጨምራል፤ የልብ መምታትን ያፋጥናል፤ የሆድ ድርቀት ያመጥል፤ የምግብ ፍላጎትን ይቀንሳል፤ መተንፈስን ያዳክማል፤ ጉበትን ይጎዳል፤ ጥርስንም ያበላሻል። ስለጫት በይበልጥ ለማወቅ ካሰፈለገ፤ ደራሲው ከዚህ በፊት የጻፋቸው ጽሁፎች በተለያዩ የኢትዮጵያዊያን ድህረ ገጾች ላይ ይገኛሉ።
ትንባሆ፦ ባጭሩ ትንባሆ አዓምሮ ላይ ከሚያመጣው የንቃት ስሚትና ሱስ በተጨማሪ፤ የደም ድዛትን፤ የልብ ህመምን፤ የሳንባ በሽታን፤ የተልያዩ የካንሰር አይነቶችንና የጥርሰ መበላሸትን ሊፈጥር ዓንደሚችል ተመዝግባል። ትንባሆ በኢትዮጵያዊያን በብዛት የሚወሰደው በሲጋራ መልክ በማጨሰ ነው።
በሳንባ በኩል የሚወሰዱ ሊሎች ኪሚካሎች፦ ዓነዚህ ሱስ አምጪ ኪሚካሎች በአፍ ውይም በአፍንጫ ተሰበው በሳንባ በኩል ሰውነት ውሰጥ የሚገቡ ናቸው። ኪሚካሎቹ በብዙ መንገድ በሰዉነት ዉሰጥ የሚሰሩ ወይም ጉዳት የሚያመጡ ናቸው። ብዙዎቹ ዓንደተወሰዱ ወዲያውኑ የአዓምሮ ንቃት ይሰጡና ቀትሎም ማደንዠዝን፤ ራሰማታትን፤ ማቅንሽንሽን፤ መንገዳገድን፤ መደበርን፤ መርሳትንና የልብና የነርቭ በሽታዎችን ያሰከትላሉ። በስፋት ከሚገኙት ኪሚካሎች መካከል በምሳሊነት የዓቃ ማይይዣ (ግሉ)፤ የግድግዳ ቀለሞ መበጥበጫ፤ የጸጉር ሰፕሪይ፤ ቢንዚን (ጋዝ)፤ ዓንደ ቡቲን ያሉ ጋዞችና አንዳንድ ተናኝነት ያላቸው የላቦራቶሪ ፈሳሽ ኪሚካሎች የሚጠቀሱ ናቸው። አስፈላጊው ጥንቃቂ ካልተወሰደ ዓነዚህ ነገሮች የልብንና የሳንባን አሰራር በማቃወሰ ድንገተኛ ሞት ሊያመጡ የሚችሉ ናቸው። ለረጅም ጊዚ ሲወሰዱ ደግሞ የአዓምሮን የማሰብ ችሎታና የአይንን የማየት ብቃት ይቀንሳሉ፤ በሰውነት ላይ ክሳት ያሰከትላሉ፤ የአጥንት ቅልጥምም ዓንዲበላሽ በማድረግ በደም አስራርና አገልግሎት ላይ ችግር ይፈጥራሉ።
በሀኪም የሚታዘዙ ሱሰ ሊያመጡ የሚችሉ መድሃኒቶች፦ ለጭንቅላት/ለራስ በሽታዎች ተብለው ህኪም የሚያዛቸው ብዙ መድህኒቶች በተክክል ከጥቅም ላይ ካልዋሉ፤ ሱስንና ሊሎች ብዙ ችግሮችን ሊያመጡ የሚችሉ ናቸው። ከነዚህም መካከል አደንዛዥ መድህኒቶች፤ ዓንቅልፍ አምጪ መድሃኒቶች፤ አንቂ መድሃኒቶች፤ የመንቀዥቅዥ ማረጋጊያ መድሃኒቶች፤ የስጋት ማስታገሻ መድሃኒቶችና የህመም ስሚት ማብረጃ መድሃኒቶች ይገኙበርታል። መድሃኒቶቹ ያለአግባብ ከተወሰዱ፤ አንደአይነታቸው የተለያዩ የአዓምሮና የሊላ የአካላት ችግር ያመጣሉ። በዚህ ርአስ ስር ሊጠቃለሉ የሚችሉ ዓንደ ባርቢቹሪት፤ ቢንዞዲያዚፕን፤ ኦፒዮይድስ አምፊታሚን የመሳሰሉ መድሃኒቶች ናቸው።
ከላይ ከተዘርዘሩት መሰረታዊ ጊዳዮች በተጨማሪ ሱስ አምጪ ስለሆኑ ነገሮች ቀጥሎ የተመለከቱት መታወቅ ይኖርባቸዋል። ማናቸዉም መድሀኒት ወይም ኪሚካል በብዛትና ለረጅም ጊዚ ሲወሰድ ጉዳቱ ከፍተኛ ይሆናል። የተለያዪ መድሃኒቶች/ኪሚካሎች ተደባልቀው ሲወሰዱ ደግሞ ያለተጠበቀ ጊዳት ሊያመጡ ይችላሉ። ሱስኞች የሚወስዳቸው ብዙ ሱስ አምጪ ነገሮች ቁጥጥርና ጥራት ስለሚጎላቸው፤ ያልታወቁ ተጨማሪ ጉዳቶች ይኖራቸዋል። በተጨማሪም በመርፊ መልክ የሚወስዱት መድሃኒቶች/ኪሚካሎች በወሳጁ ላይ ዓንደ ኢቻአይቪ/ኢይድስና ሂፓታይተስ የመሳሰሉ በሽታዎችን ሊያስተላልፉ ይችላሉ።
በዚህ ጽሁፍ የተገለጹትንም ሆነ ሊሎች ሱስ አምጪ የሆኑ ነገሮችን ለመቆጣጠርና በአግባብ ከጥቅም ላማዋል ወይም ጥቅም የሊላቸዉን ለማስወገድ፤ በተልያዩ አገሮች የወጡ ደንቦች አሉ። በአሚሪካ ዓነዚህ መድሃኒቶች/ኪሚካሎች ባአንድ ላይ “ቁጥጥር የሚደረግባቸው ቁሳቁሶች” በመስለ ስያሚ ታዉቀው በሚያመጡት የሱሰ አይነትና በሊላ መለኪያዎች ተገምግመው በአምስት ክፍል ተዋቅረዋል። ከዚህ አመዳደባቸውጋር በማገናዘብ መድሃኒቶቹን/ኪሚካሎቹን ከህግ ዉጪ ለሚጠቀሙ፤ ለሚሰሩ ወይም ለሚያሰራጩ ሰዎች ተመጣጣኝ የሆኑ ቅጣቶች ደመድበዋል። ሰለዚህ ከዓነዚህ ሱሰ አምጪ ነገሮች ዓራስን በተቻለ መጠን ማራቁ፤ በሰዉነትም ሆነ በኢኮኖሚ ላይ ሊያመጡ ከሚችሉት ጉዳት መትረፍ ብቻ ሳይሆን ከወንጀልና ከቅጣትም መዳን ሊሆን ይችላል።
በመድሃኒቶችና በሊላ ተመሳሳይ ነገሮች ሱሰ ላለመጠመድ ዓነዚህን ነገሮች መዉሰድ አለመጀምሩ ከሁሉ በላይ የሚመረጥ ነው። ነገሮቹ ከተወሰዱ በወሳጁ ላይ ሊያመጡ የሚችሉትን ችግሮች በቅድሚያ ማወቁ ለመከላከሉ ዉሳኒ የሚረዳ ነው። ስለዚህ ችግሩን በቅድሚያ ለመከላከል ትምህርት ወሳኝ ነው ለማለት ይቻላል። በቁሳቁሶቹ ሱስ ለተጠመደ ሰውም ቢሆን ሊረዱ የሚችሉ ልዩ ልዩ አገልግሎቶች አሉ። ፈቃደኛ ለሆነ ሱሰኛ የባለሞያ ስነልቦናዊ ምክር ማግኝት፤ የድጋፍ ክለብ አባል መሆንና የህክምና ባለሞያ ዓርዳታ ማግኘት የሚቻል ነው። ዓነዚህና ተመሳሳይ የሆኑ ዓርምጃዎች በየፈርጁ መልካም ውጢት ያሰገኙ ናችው። አሁንም ዓንደገና የተጠቀሱትን አገልግሎቶች በትክክል ለማወቅና ለመጠቀም፤ ስለ ሱሰ አምጪ ቁሳቁሶች ቢያንሰ የተወሰ ትምህርት ማግኘቱ ዓጅግ ጠቃሚ ነው።
ጥረት ከተደረገ ከሱስ ተገዢነት ነጻ መውጣት የሚቻል ነው። ችግር ያለባቸው የመጪው አዲስ ዓመት ይህ አንዱ አላማቸው ዓዲሆን በመጠየቅ፤ 2013 መልካም ዓመት ዓንዲሆንላቸው ዓመኛለሁ።