(ሰበር ዜና) የኢትዮጵያ መንግሥት ለብፁዕ ወቅዱስ እንዲመለሱ ፈቀደ፤ ፕሬዚዳንት ግርማ ደብዳቤ ጽፈዋል

(ደጀ ሰላም ኅዳር
26
/2005 ዓ.ም፤ ዲሴምበር 5/2012/ PDF)፦ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቀርዮስ ወደ መንበራቸው እንዲመለሱ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ
ዲሞክራሲያዊት ሪፓብሊክ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ መመሪያ ሰጡ::
ፕሬዚዳንት ግርማ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን
4ኛ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ወደ ሃገር ቤት ተመልሰው ከሁለት የተከፈለችው ቤተ ክርስቲያን አንድ እንድትሆን
የሚያሳስብ ደብዳቤ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ እና ለብፁዕ አቡነ ናትናኤል መጻፋቸውን የደጀሰላም ምንጮች
አረጋግጠዋል:: የሰላም ጉባኤው በሚጀመርበት
ዕለት ይህ ደብዳቤ
መጻፉ
ዝበ ክርስቲያኑ በከፍተኛ
ጉጉት እየተከታተው ያለውን እርቀ ሰላም ተፈጻሚ ያደርጋል ተብሎ ይታመናል:: ፕሬዚዳንቱ ይህን ደብዳቤ የጻፉት የሰላምና አንድነት
ጉባኤው ለመንግስት ጥያቄ አቅርቦ ይሁን ወይንም በሌላ የታወቀ ነገር የለም:: 
ዝርዝሩን እንደደረሰን እናቀርባለን::                                                                                                       
 “ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተ
ክርስቲያን – ስለ ቤተ ክርስቲያን ሰላም ጸልዩ”።
ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡