ዓቃቤ ሕግ በሽብርተኝነት የተከሰሱት 29 ተጠርጣሪዎች ያቀረቡት መቃወሚያ ሕጋዊ መሠረት የለውም አለ

–    የአቶ ጁነዲን ባለቤት ክስ ከሌሎቹ እንደማይለይ ተገለጸ

በታምሩ ጽጌ

የእምነት ነፃነትን በመቃረን ከራሳቸው አክራሪ አስተሳሰብና አስተምህሮት ውጪ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ሌላ እምነት መኖር የለበትም በሚል ሃይማኖታዊ መንግሥት ለማቋቋም ፖለቲካዊ ግብ በማስቀመጥ፣ በሕገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተደርሶባቸዋል በሚል በሽብርተኝነት ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸው 29 ተከሳሾች ያቀረቡት የክስ መቃወሚያ፣ የሕግ መሠረት የሌለው ነው በማለት ውድቅ እንዲደረግ ዓቃቤ ሕግ ጠየቀ፡፡