ሁለት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ተሾሙ

–    ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆኑ
–    አቶ ጁነዲን ሳዶ ተነሱ

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በዛሬው ዕለት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረቧቸው የሁለት ጠቅላይ ሚኒስትሮችና የሌሎች ሚኒስትሮች ሹመት ፀደቀ፡፡ በፀደቀው ሹመት መሠረት ለምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት የተሾሙት የኢንፎርሜሽንና ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤልና የካቢኔ ጽሕፈት ቤት ኃላፊው አቶ ሙክታር ከድር ናቸው፡፡