የሱሉልታ ከተማ ኢንቨስትመንት ባለሥልጣናት ጉቦ ሲቀበሉ ተያዙ

–    የወረዳው ሥራ አስኪያጅ በእስራትና በገንዘብ ተቀጡ

በታምሩ ጽጌ

በኦሮሚያ ልዩ ዞን የሱሉልታ ከተማ ኢንቨስትመንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዮሴፍ ጌታቸውና የከተማው ማዘጋጃ ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ መሸሻ ዘውዴ፣ 200 ሺሕ ብር ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ፡፡