ናይል ኢንሹራንስ በአቢሲኒያ ባንክ ካለው አክሲዮን 17.7 ሚሊዮን ብር ሊቀንስ ነው
በዳዊት ታዬ
ከ1983 ዓ.ም. ወዲህ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የግል ኢንሹራንስ ኩባንያ በመሆን የተቋቋመው ናይል ኢንሹራንስ አክሲዮን ማኅበር፣ በብሔራዊ ባንክ መመርያ በአቢሲኒያ ባንክ ውስጥ ካለው 49,217,600 ብር ከሚሆነው አክሲዮን ውስጥ 17,717,600 ሚሊዮን ብር ዋጋ ያላቸውን አክሲዮኖች ሊቀንስ ነው፡፡