ከፍተኛ የፖታሽ ምርት ለማምረት የተዘጋጀው አላና አቅሙን እያፈረጠመ ነው

–    ፖታሽ የኢትዮጵያ ዋነኛ የውጭ ምንዛሪ ማስገኛ ይሆናል እየተባለ ነው

በዳዊት ታዬ

ከአንድ ዓመት ተኩል በኋላ የአገሪቱ ዋነኛ የወጪ ንግድ ማስገኛ ይሆናል የተባለውን የፖታሽ ማዕድን ለማምረት በዝግጅት ላይ የሚገኘው አላና ፖታሽ የተባለው ኩባንያ፣ በኢትዮጵያ በተመሳሳይ ሥራ ላይ የተሰማራውን ኖቫ ኢትዮ ፖታሽ ኮርፖሬሽን የተባለውን ኩባንያ ጠቀለለ፡፡