በአፋር ክልል ኢንቨስተሮች መሬት በአግባቡ አናገኝም ማለታቸውን የክልሉ መንግሥት አጣጣለው

‹‹ከጐሳዎች የመሬት ባለቤትነት ጋር በተያያዘ በኢንቨስተሮች የሚነሳው ቅሬታ መሠረተ ቢስ ነው›› አቶ ኢስማኤል አሊሴሮ፣ የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዚዳንት

በምሕረት አስቻለው

ከኢንቨስትመንት ጋር በተያያዘ በክልሉ የአገሪቱ የመሬት ፖሊሲ በአግባቡ ሊተገበር ባለመቻሉ በጐሳ መሪዎች የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ ችግር ውስጥ ወድቀናል የሚሉ ኢንቨስተሮች ቅሬታ መሠረተ ቢስ መሆኑን የአፋር ክልል አስታወቀ፡፡