የግብፅ መንግሥት በዓባይ ጉዳይ ባለሥልጣናቱ የሚሰጡት መግለጫ እንደማይመለከተው አስታወቀ
– ለኢትዮጵያ መንግሥት በደብዳቤ ማብራሪያ ሰጥቷል
በዮሐንስ አንበርብር
የግብፅ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት በአገር ውስጥና በተለያዩ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን የዓባይ ወንዝን በተመለከተ በግብፅና በኢትዮጵያ ወቅትታዊ ሁኔታ ላይ በተከታታይ የሚሰጡት መግለጫ እንደማይመለከተው የግብፅ መንግሥት ለኢትዮጵያ መንግሥት አረጋገጠ፡፡