ከ160 በላይ ኢንዱስትሪዎች ከመልቲ ሞዳል ውጪ መስተናገዳቸው ለአሠራሩ መጨናገፍ ጠቋሚ መሆኑ ተነገረ

በብርሃኑ ፈቃደ

የኢትዮጵያ ገቢና ወጪ ዕቃዎችን በፍጥነት ለማስተናገድ ያስችላል የተባለውን የመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት መመርያ ያወጣው የትራንስፖርት ሚኒስቴርና የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪው ችግር ያሳሰበው ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ ኢንዱስትሪው በዩኒሞዳልም ሆነ በመረጡት መርከብ ድርጅት  ዕቃዎቻቸውን ወደ አገር ውስጥ እንዲያስገቡ በማሳሰብ ለ164 ያህል ግዙፍ ኢንዱስትሪዎች ከመልቲ ሞዳል ውጪ እንዲስተናገዱ ትዕዛዝ በመሰጠቱ ምክንያት፣ ሥርዓቱ በተዘዋዋሪ መንገድ ከመጓተት አልፎ እየተጨናገፈ መሆኑን የሪፖርተር ምንጮች ገለጹ፡፡