ፕሬዝዳንት ኦባማ በሁለተኛውን ዙር ምርጫ ምን ይጠበቅባቸዋል
ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ)
ፕሬዝዳንት ኦባማ ሁለተኛውን ዙር የፕሬዝዳንትነት ምርጫ በማሸነፋቸው እንኳን ደስ ያለዎት ማለቱ አግባብ ነው። የአሜሪካንን መራጮች አብላጫ ድምጽ አግኝቶ ለማሸነፍ ብቃት ባለው አካሄድ ለድል በቅተዋል። ሚት ሮምኒም ለማይናቀው የምርጫ ግብግባቸው ሊመሰገኑ ተገቢ ነው። በማጠቃለያው የመለያያ ንግግራቸው ላይ ሚት ሩምኒ ግሩም የሆነ መልእክት አስተላልፈዋል።