ትንሽ ወግ ስለደምሴ ዳምጤ

አያልቅበት አደም

የደምሴን መታመም ከሰማሁ ወዲህ ያደረበት የስኳር ሕመም (ዲያቤቲክስ) የዓይኑን ብርሐን ከማሣጣት በዘለለ ይህን ያህል ለሕይወቱ ያሰጋል ብዬ አልገመትሁም። ለመጀመሪያ ሕክምና ወደ ባንኮክ ተጉዞ ሲመለስ የአንደኛው ዓይኑ ብርሐን ማጣት አስከፊ ዜና ቢኖርም የቀኝ ዓይኑ ብርሐን ወደ 20 ከመቶ የተመለሰ መሆኑንና ሊሻሻል እንደሚችል በመስማቴ ተመስገን ብያለሁ።