ፍርደኛው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እንዲወረስ ጥያቄ በቀረበበት ንብረቱ ጉዳይ አልከራከርም አለ
– አቶ አንዱዓለም አራጌም ፍርድ ቤት ቀርበዋል
በታምሩ ጽጌ
በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሶ በ18 ዓመታት ፅኑ እሥራት እንዲቀጣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ውሳኔ ያሳረፈበት ፍርደኛው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ዓቃቤ ሕግ እንዲወረስ ስለጠየቀበት የንብረት ጉዳይ ቤተሰቡም ሆነ እሱ መከራከር እንደማይፈልጉ ለፍርድ ቤቱ አስታወቀ፡፡