የባንኮች ማኅበር ቦርድ ፕሬዚዳንቱንና ምክትል ፕሬዚዳንቱን በድጋሚ መረጠ

–    የባንክ ኢንዱስትሪውን የሚመለከት የሬዲዮ ፕሮግራም ሊጀመር ነው

በዳዊት ታዬ

በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ የሚንቀሳቀሱትን ሁሉንም የመንግሥትና የግል ባንኮች በአባልነት የያዘው የኢትዮጵያ ባንኮች ማኅበር አቶ ብርሃኑ ጌታነህንና አቶ በቃሉ ዘለቀን ለሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ማኅበሩን በፕሬዚዳንትነትና በምክትል ፕሬዚዳንትነት እንዲመሩ በድጋሚ መረጠ፡፡