አንድ ማስታወሻ ለጋዜጠኛ ደምሴ ዳምጤ

ጋዜጠኛ ደምሴ ዳምጤ, Journalist Demissie Damteመስፍን ነጋሽ

በእኔ እድሜ የደምሴን ያህል አገራዊ የስፖርት ስሜትን፣ በተለይ እግር ኳስን ወደ ልባችን ያቀረበ ጋዜጠኛ አልነበረም። እንደዛሬው ኢንተርኔት መገልበጥ ማእረግ በማያሰጥበት ዘመን። በሳምንት ሁለትና ሦስት ቀን ስታዲየም በምገባበት፣ ሁለቱን ሙሉጌታዎች፣ እነሚሊዮን በጋሻውን፣ እነቸርኬን (ጊዮርጊስ)፣ እነሙሉዓለም እጅጉን (ጦሩ)፣ እነአብዲን (መድን)፣ እነአፈወርቅን (እርሻ)፣ ያ ደሞ የአየር ኀይሉ አጥቂ ማን ነበር? … ረሳሁት ማለት ነው? (ይልቅ ተከላካያቸው መሰለ፣ ጆን ቴሪን ቁጭ ነበር)፣ ከዛ ደሞ … ይህ ሁሉ ሲሆን ብቸኛው የስፖርት መረጃ ምንጫችን ደምሴ ነበር፤ እርግጥ ሌሎችም ጋዜጠኞች ነበሩ በተለይ እነ … ማነው … ይንበርበሩ መሰለኝ። ቢሆንም ደምሴ የተለየ መስህብ ነበረው።