የብሔራዊ ስሜት – አብነት!
ሰሎሞን ተሰማ ጂ.
ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነውን DC-6 B አይሮፕላን፣ መስከረም 3 ቀን 1962 ዓ.ም. በሶሪያ የወንበዴዎች ቡድን (ጀብሃን ለማለት ነው) ተገድዶ ኤደን ባረፈ ጊዜ፣ የመንገደኞቹን ሕይወትና አይሮፕላኑንም ከቃጠሎ ያዳነው ም/አለቃ ካሳዬ ታደሰን የያዘው አይሮፕላን ከድሬዳዋ አዲስ አበባ፣ ትናንት ጥቅምት 3 ቀን 1962 ዓ.ም በዘጠኝ ሰዓት ተኩል ገብቷል። ቀድሞ በምድር ጦር ውስጥ ምክትል የአስር አለቃ የነበረውና አሁን በሲቪል አቪዬሽን ውስጥ የበረራ ደኅንነት ኢንስፔክተር የሆነው ካሳዬ ታደሰ ከቦሌ አይሮፕላን ማረፊያ በቀጥታ ወደ ኢዮቤልዩ ቤተ መንግሥት ኼዶ፣ ግርማዊ ንጉሠ ነገሥት ዘንድ ቀርቧል።