ትውልደ ኢትዮጵያዊያን አሜሪካውያን በ2012 ምርጫ መሳተፍ ይገባቸዋል

ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
(ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ)
ጉዳዩ የምርጫ ብቻ አይደለም እኮ!
ባለፈው ሴብቴምበር ስለ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ድጋሚ መመረጥ ድጋፌን ገልጬ ነበር። ለታዳሚዎቼ እንዳስነበብኩት በ2008 ምርጫ ተወዳዳሪ ባራክ ኦባማን ደግፌ እንደነበርና ከምርጫው በኋላ ግን በታየው በተለይም ኢትዮጵያንና አፍሪካን በተመለከተ ስለተካሄደው አስተዳደራዊ ፖሊሲ ግን በጣሙን ቅሬታ አድሮብኛል።