አቡነ ቴዎድሮስ፤ 118ኛው የግብጽ ኮፕት ፖፕ ሆኑ
(ደጀ ሰላም ጥቅምት 25/2005 ዓ.ም፤ ኖቬምበር 4/2012/ READ IN PDF)፦ የግብጽ ኮፕት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዛሬ ጥቅምት 25 ወይም ኖቬምበር 4 ባደረገችው የዕጣ ማውጣት ሥርዓት ብፁዕ አቡነ ቴዎድሮስን 118ኛው ፖፕ እንዲሆኑ ሰይማለች፡፡ በቀጥታ የቴሌቪዥን ሥርጭት ሥርዓቱ ለመላው ዓለም በተሰራጨበትና ዓይኑን በጨርቅ የተጠቀለለ ሕጻን ዕጣውን ባወጣበት ሥርዓት “አቡነ ቴዎድሮስ” 118ኛው ፓትርያርክ ሆነው ተመርጠዋል። የግብጽ ቤተ ክርስቲያንን ላለፉት 40 ዓመታት የመሩት 117ኛው ፖፕ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ እንደነበሩ ይታወሳል።
ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡