የሙስሊሞች እንቅስቃሴ ክፍል 1 – ምላሽ ለዶ/ር ብርሃኑ

አማኑኤል ዘሰላም

መግቢያ

ከእስልምና ጉባዔ ምርጫ ዙሪያ፣ በወሎ ክፍለ ሃገር ፣ ሀገራ ከተማ በተነሳው ግጭት ሶስት ኢትዮጵያውያን ሕይወታቸው እንዳለፈ ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል። ምርጫው ከተደረገ ከበርካታ ቀናት በኋላ፣ በምርጫ በተሳተፉትና በምርጫ ባልተሳተፉት መካከል የተነሳውን ግጭት ለማብረድ ፖሊስ ጣልቃ እንደገባ የዘገበው ሪፖርተር፣ ከሞቱት ሰዎች መካከል አንዱ የፖሊስ አባል እንደሆነም ጠቅሷል።