አቶ ኃይለማርያም እና ኤርትራ – መልስ ለአቶ ግርማ ካሳ
አቡጊዳ ቀይሶ ከኮልፌ
ውድ አቶ ግርማ ካሳ “አቶ ኃይለማርም እና ኤርትራ” በሚል ፅሑፍ አዘጋጅና አቅራቢ በመሆን ያለዎትን ሃሳብ ስላካፈሉን በቅድሚያ ያለኝን ምስጋናዬ ላቅርብ። በፅሑፎ ላይ ስለሰጡት የዘር መተንትን ከእርሶ ጋር የምጋራው ነጥብ ቢኖረኝ እንጂ የምቃወምዎት ሃሳብ የለኝም። ምክንያቱም ዘር የእድል ጉዳይ እንጂ የጥረት ውጤት አይደልምና። ማንኛውም ሰው መመዘን ካለበት በጥረቱ በሚሰራው ስራና በሚያመጣ ውጤት እንጂ በዘር መሆኑ በጣሙን የተሳሳተ አመለካከት በመሆኑ በዚህ ላይ ሰፊ ትንታኔ መስጠት ቢቻልም በግዜው ስለፃፉት ስለ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃሳብ ላይ ያለኝን አስቴየት ለመሰንዘር ነው።