ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የጠየቀው ይግባኝ ተቀባይነት በማግኘቱ ለክርክር ተቀጠረ

–    ጠበቆቹን አሰናብቶ ራሱ ይከራከራል

በታምሩ ጽጌ

በተከሰሰበት የሽብርተኝነት ወንጀል ጥፋተኛ ተብሎ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ሰኔ 20 ቀን 2004 ዓ.ም. በ18 ዓመታት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ውሳኔውን በመቃወም ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረበው ይግባኝ ተቀባይነት በማግኘቱ ለክርክር ለጥቅምት 27 ቀን 2005 ዓ.ም. ተቀጠረ፡፡