ለአቶ በፈቃዱ በቀለ የተስጠ ምላሽ በከፍያለው ገብረመድህን

የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) በመተዳደሪያ አንቀጹ ቁጥር IV ሥር ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የሚያድርገውን ውይይት ሲያጠናቅቅ ባወጣው ሪፖርት ላይ ተመሥርቼ Ethiopia & IMF: Drawing lances or lines? በሚል ርዕስ ጥቅምት 2፤ 2012 አቡጊዳ ላይ ላቀረብኩት ጽሑፍ አቶ በፈቃዱ በቀለ የሰጡትን አስተያትት ዛሬ ጥዋት ለመመልክት ዕድል አግኝቼአለሁ።

አስተያቶችንና ግንዛቤዎችን መለዋወጥ የሚኖራቸውን ጠቃሚነት አበክሬ ስምገነዘብ፡ ከዚያ አንጻር ግለስቡን ለአስተያታቸው ከልብ አመስግናለሁ። በተለይም የሰነዘሩት አስተያየት የሃሳብ ጨዋነትን የተላበስ ቢሆን ኖሮ ይበልጥ ጠቃሚ ሊሆን እንደሚችል በቅድሚያ ላስታውስ እወዳለሁ።

የተቺው አመለካከት በአይዲኦሎጂ አሰከባሪነት የተጠመቀ በመሆኑ፡ የትችቶቻቸውም ይዘት በዚያው የተመሩ ናቸው። የተነሱትን ጉዳዮች በተለይም የመንግስት ፖሊሲ ዋነኛው ጉዳይ ሆኖ ሳለ የእርሳችውን አስተያት ሳይሰጡ ማለፋችው ቢገርመኝም፡ ብዙ ሳልቆይ ምክንያቱን ለማወቅ ችያለሁ – ወደቀላሉ ነገር አዘንብለው፡ ሲተቹ ዋናውን ቁም ዘነጉት። መንግስትነም ሲተቹ እንዲህ ሲሉ ይያያዙታል – “የወያኔ መንግስት ዘራፊ መንግስት ነው። የሚያካሂዳቸው ፖሊሲዎች በሙሉ በምንም ዐይነት ከሳይንስ ጋር የሚጣጣሙ አይደሉም።”

ይህን የምሁር ትንተና ነው ብዬ ጊዜያን አላባክንበትም። በመሆኑም ከዚህ ውጭ አንዳችም የፖሊሲ ትንተና አለመስንዘራችው ቅር አስኝቶኛል።

በዚህም ምክንያት በቅድሚያ ያጠናገሩትንና ከእኔ ጋር አያይዘው በከንቱ ያንገላቱትን የሪፖርቱን መልዕክት ላስታውሳችው እሞክራልሁ። ከዚያም ግልሰባዊ እምነቴንና አመልካከቴን በሚመለከት የሰነዘሩትን ደረጃው ያዘቀጠ ታፔላ የመለጠፍ ጥረታቸውን፡ ተወዳጅና በአገራችን ታዋቂ በሆነው ነዋሪ አባባል -”መልዕክቱን ትቶ መለዕክተኛውን ማክስል” ከእርሳቸው የማይጠበቅ መሆኑን በማስታወስ፤ ሰበቃችውን በትዕዝብት ቦታውን ለማሳየት እሞክራለሁ።

ለመሆኑ ምንድናቸው የአቶ በፈቃዱ ዋና ዋና ትቶች? እንዳልሳሳት እርሳችው እንደጻፉዋችው እጠቅሳቸዋለሁ፦

• “በመጀመሪያ ደረጃ የአቶ ከፍያለውን ጽሁፍ ለተከታተለ ሰውየው የኒዎ-ሊበራል አጀንዳን ነው _የሚያስተጋባው።

• በሁለተኛ _ደረጃ፣ _በተለይም ይህ ጽሁፉ በምንም ዐይነት የሳይንስን ስታንደርድ የጠበቀ አይደለም። ከተጨባጭ ሁኔታ በመነሳት የነገሮችን ዕድገትና ዛሬ የደረሱበትን ሁኔታ በጥልቀት ለመተንተን_የሚቃጣ አይደለም።

• በሶስተኛ ደረጃ፣ ጸሀፊው ሊያሳምነን እንደሚሞክረው ባለፉት 21 ዐመታት በኢትዮጵያ ምድር ተግባራዊ የሆነው የኢኮኖሚ ፖሊሲካለ አይ ኤም ኤፍ ተሳትፎ ውጭ ነው የሚለን ነው።”
ድምዳሜያቸው ደግሞ አሁንም እንዳልሳሳት እርሳችው እንደጻፉዋችው እጠቅሳቸዋለሁ፦ ፦

• “ይህ በጥሩ እንግሊዘኛ ተቀነባብሮ የቀረበው የአቶ ከፍያለው ጽሁፍ በመጀመሪያ ደረጃ፣ የኢትዮጵያን ህዝብ ጥቅም በምንም_ዐይነት የሚያንፀባርቅ አይደለም።

• በሁለተኛ ደረጃ በማንኛውም ሳይንሳዊና ኢምፔሪካል ጥናት የሚደገፍ አይደለም።

• በሶስተኛ ደረጃ፣ ብዙ ታዳጊ ወጣትን የሚያሳስት ነው።”

የመጀመሪያው የአቶ በፈቃዱ ትችት “የኒዎ-ሊበራል _አጀንዳን” አራምደሃል በማለት የተስነዘረው ክስ መሠረተ ቢስ ነው። ይህ አባባል እራሳችውን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ፊታውራሪና ተቆርቋሪ አድርገው ሲከራከሩ ከከረሙ (ባልሳሳት) ኢኮኖሚስት ሲመጣ፤ ያለንበትን ማጥ ጥልቀት የሚያመላክት ከሆኑም በላይ በአይዲኦሎጂ ጥራት ትኩረት መፈነካከት አገራችንን ሊያጋጥሟት ከሚችሉ ችግሮች አንዱ እንዳይሆን እስጋለሁ።

የኢትዮጵያ መንግሥት ነጋዴና የግሉ ዘርፉ አይታመኑም ብሎ ከሕዝቡና ከግል ዘርፉ ገንዘብ እያስባስበ (በግዳጅ) በመንግስት የልማት ድርጅትች አማከይነነት በአብዛኛው ፍሬ አልባ በሆነ አቅጣጫ ሁሉ ሲበተን እንድ ጥሩ ፖሊሲ መመልክት አልሻም። አይ. ኤም. ኤፍም የአስተሳስቤ ገንባታ ማዕዘን ባይሆንም፤ በትክክል ያለው – “The planned significant domestic financing of the GTP could result in a deceleration of medium-term growth and a buildup of vulnerabilities absent the necessary policy adjustments.”
ተቺው ግለስብ ይህንን እንደመልካም ምክር ካላዩት፤ ለእርሳቸው የሰጣችው መለዕክት ‘ልማታዊው መንግሥት’ አደጋ ላይ መሆኑን ከሆነ ልዩነታችን ጥልቅና ዘላቂ ነው። ኤኮኖሚስትእንደመሆናቸው ይሀ ሎጂክ ለምን እንደመረራችው መገመት ያዳግተኛል።

እኔ እንድምገንዘበው፤ አይ. ኤም. ኤፍም. እንደሚለው መንግሥታዊ ድርጅቶችን አቋቁሞ ለልማት መጠቀም ጥሩ ቢሆንም፤ የዚህ ዐይነት ፖሊሲ ተገባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታና አካሄድ ኢትዮጵያ ውስጥ በብቃት በሌለበት (ተቋምች፡ ጥራትና ብቃት ያለው የሰለጠነ የሰው ኀይል)፡ እንዲሁም የሕግ የበላይነት በማይከበርበት አገርና ግልጻዊነት በሌለበት ሁኔታ ዕድገትን ለዘለቄታው በሚያስፈልገው ፍጥነትና ኤፊሽንሲ ውጤታማ ማድረግ እንደማይቻል ነው። አገሪቷም ከሌሎች አገሮች ጋርበተወዳዳሪነት ውጤት ማሳየት ያዳግታታል።

በሌላ አነጋገር፤ ገንዘብ ቢዶልም የሚፈለገው ልማትና ለውጥ ተገኝቶ የብዙኅኑ ዜጎች ኑሮ አይሻሻልም! እንደውም ኮረፕሽን ይጠናከራል።
ለምሳሌ በዘመናዊ ተሌኮም አገራችን ኋላቀር ናት። በዚያ መስክ እስካሁን የፈሠሠው አያሌ የአገር ሀብት በነጻ ሃሳብን መለዋውጥንና የመናገርን ነጻነት ከማፈን ውጭ ያተረፈን ነገር ቢኖር የአገራችንን በቴክኖኦሎጂና ፖለቲካ ኋላ ቀርነቷን ማጋለጡ ነው። ለማስረጃ ያህል፡ ሰሞኑን የወጣው የአይ. ቲ. ዩ. (International Telecommunications Union) ሪፖርት ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ከ154 አገሮች መካከል በ 2010 እና በ 2011 በ150ኛ ደረጃ ከኋላዋ ቦርኪናፋሶን፡ ኤርትራን፡ ማዕከላዊ አፍሪቃን፡ ቻድንና ኒጀርን አስከትላ እንደምትገኝ ይመሰክራል።

ለሳምንታት የሕወሃት ምክትል ሊቀመንበርና የቴክኖሎጂ ሚኒስትር ደብረጽዮን ሕዝቡን ሲያደነቁሩ የነበሩት ኢትዮጵያ ምን ያህል በቴክኖሎጅ እንደተስፈነጠርች ነበር። ነገር ግን ባለፉት 21 ዓመታ አገሪቱ ውስጥ ከአሜሪካው ሲሥኮ ኩባንያ፤ እስክስዊድኑ ኤሪክሰን፤ የፊንላንዱ ኖክያ ዛሬ ደግሞ የቻይናው ሁዌና ዚ.ቲ.ኢ. የተንሰራፉባት አገር ሆና ሳለ አሁንም የአፍሪቃ ጭራ እየሆነች መምጣቷን ነው።
ብዙ ገንዝብ ፈሷል፤ በብዙ ሽህ የሚቆጠሩ ሠራተኞች ያለምንም ድጋፍ ተበትነዋል። የሞባይል ስልክ ተጠቃሚው ቁጥር በአቶ ደብረጽዮን መረጃ መሠረት 18 ሺህ ደረስ ቢባልም፤ ዛሬም አገራችን ዓለም አቀፉ የቴክኖሎጂካል መገናኛ መሥመር (Information Communication superhighway) ውስጥ ገብታለች ለማለት አይቻልም።

ቤይጂንግ እይሳቀችና እያሳቀች፡ አንዳንዴም ብድርና ማጣፈጫውን እያቃመች: እንዴት እንደምትመዘምዘን አንድ ምሁራዊ አዝማሚያ ያለው (Caixin Online) የተስኘ የቻይና ጋዜጣ ማጋለጡን ማስታወሱ ይበቃል። ለማንበብ እዚህ ይጫኑ።

በመብራት ኅይል ረገድ ብዙ የግንባታ እርምጃዎች ቢወስዱም፡ አሁንም አብዛኛው ሕዝባችን በጭለማ መጋረጃ ውስጥ ነው። ይባስ ብሎ አቶ ኃይለማርያም ባለፈው ማክስኞ ፓርላማ ቀርበው፡ አገራችን ጭለማ ውስጥ ብትሆንም መብራት ወደ ውጭ የሚሸጥበትን ምክንያት ቅዱስነት ለማስጭበጥ ሲፍረከረኩ መመልከቱ አሳዝኝ ከመሆኑም በላይ፤ ተቺው በትክክል የነካኩት የውጭ ምንዛሪ የማግኘቱ ትንቅንቅ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ነው። ለዚያውም አቶ ኃይለማሪያም የሰነዘሩት የውጭ ምንዛሪ የለብንም የሚለው ክህደት የሚታየውን የአካውንቶች መዛባት እንዴት እንደሚሽፋፍኑት ማየት ያጓጋጓል።

በነገራችን ላይ የአባይ ዳም ሲታስብና ሲጀመር ክመጀምሪያው ደጋፊዎች መካክል ነበርኩ። በይበልጥ እምነቴ የተመሰረተው ግንባታው በአባይ ላይ ዋስትና ይሆነናል ክሚልና ወጭውን መንግስት፤ የግሉ ዘርፉና ሕዝቡ ከኢኮኖሚው ገቢ ጋር ተዳምሮ ጊዜ ቢፈጅም ይሸፈናል ከሚል ነበር። አቶ ኃይለምሪያም ገንዘብ ቋጥረን ሳይሆን “ጥርሳችንን ነክሰን እንሰራለን ብለን ነው የተነሳነው” ከማለት ውጭ ሕዝቡ በመልካም አመራር እጦት “መማረሩን እንገነዘባለን” የሚለው አመኔታ ችግሩን በትክክለኛ መልኩ ለመግነዘብና ለመፍታተ ጥሩ መነሻ ይሆናል እላለሁ።

ዋናው አፍጥጦ ያለው ችግር በ2012 እንደታየው ከሆነ፤ ወጭው ሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎችን በተለይም የግሉን ዘርፍ ክፉኛ መፈታተኑ ነው ። የአገሪቱን የወደፊት ኢኮኖሚያዊ አሠራርና አግጣጫ አሳሳቢ እያደረገው ነው። ይህም የሆነበት ምክንያት፤ ከውጭ የሚገኝው የተፈለገው የንግድ ገቢ፡ ዕርዳታና የተጠበቀው ብድር ባለመግኘቱ፡ መንግሥት ወደ ገንዘብ ቡጥቦጣ ለመሽጋግር አስገድዶታል።
ስለሆነም የመጀመሪያ ወላፈን የገረፈው የግሉን ዘርፍ ነው። ዚጎች በአግራችው ውስጥ ሰርተው ከመጠቀምና አገራችውን ከመጥቅም ይልቅ ወደ ደቡብ ሱዳን እንዲያተኩሩ የሚያስገድዳችው ምንድነው ብሎ ማስብ ያስፈልጋል።

በተለይም መንግስት ለሕዝቡ ከበሬታ እስካሳየ ድረስ (ነጻነቱን ና መብቶቹን)፡ በሕግ እስካተዳደረ፤ ሕዝቡን አስካሳመነ ድረስ፡ እንዲሁም መስዋዕትነቱ ሁሉም ወገኖች ላይ እስካረፈ ድረስ ኢትዮጵያ አባይ ላይ ዘላቂ የመሠረት ድንጋይ (Title Deed) ማኖሯንና በውሃ ሃብቷ ተጠቃሚ እንድትሆን ደግፋልሁ። ይህ በአባይ ላይ የተወሰደው ጅምር ከግብጽ ጋር በሚደረገውም ማናቸውም ድርድር የኢትዮጵያን እጅ ያጠናክራል የሚል ውስጣዊ አስተሳስብንም የጨመረ ነበር።

ከላይ እንደተጠቀስው: ኢትዮዮጵያ አባይ ላይ ግድቡን በግል ሃብቷ ለማሰራት የምትሞክረው ስለሆነ ማንም ሊያግዳት አይችልም (ከግብጽ ጦርነት ውጭ)። አይ. ኤም ፍም መስራት አትችሉም አላለም። ሊልም አይችልም፡።

እኔ እንደተገንዘብኩት ከሆነ፤ አይ. ኤም.ኤፍም. ገዝቡን ሰብስባችሁ እዚያ ላይ ብቻ መዶላችሁ ትክክል አይደለም ነው የሚለው። ሌሎቹ የኢኮኖሚው እንቅስቃሴዎች ክፉኛ ይጎዱና፡ መንሰርራት አይቻልም ብሎ ከመስጋት የመነጭ ትክክለኛ አመለካከት ነው።
የመንግሥት የልማት ድርጅቶች አስራር የሚፈለገውን ውጤት ለማስገኘት ገንዘብ መዶል ብቻ ስይሆን የሕግ የበላይነትና ዲሞክራሲያዊ አስራር ይጠይቃል። ለምሳሌ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ2011-2012 የፊናንስ ዘመን ሥራ አፈጻጽም ክፍተኛ ውጤት አግኝቷል (ብር 7.6 ቢሊዮን ትርፍ)። ይህ የሆነው ባንኩ ለመንግስት የገንዘብ ምንጭ ስለሆነና የሚጠቀምበት በመሆኑ ሁኔታዎች እስከ ድረስ ተምቻችተውለት ነው።

በአንጻሩ ግን ይህ የፖሊሲ አስራር ቀሪዎቹን 14 የግል የንግድ ባንኮች ጎድቶአቸዋል። በመሆኑም ካብ የነበረው ትርፋቸው በ2011-2012 የፊናንስ ዘመን የመናድ አዝማሚያ እይታየበት ነው። ይህ ማለት ደግሞ የባንክ አግልግሎት ባልተስፋፋባት አገር፡ የጀመሩትን የቴክኖሎጅና የቅርንጫፍ ማስፍፋት ጉዳይ ችላ እንዲሉት ከማድረጉም ባሽገር በትርፍ እጦትና ኪሳራ ላለመስመጥ ሲሉ ከራዳር በታች ወደሚካሄዱ ተግባሮች አንዳንዶች የባንክ ባለምያዎችን ሊገፋፋችው የችላል። ይህንን በተመለክተ በቅርቡ የቅፍኩትን መመልከት የሚፈልጉ ከሆንእዚህ ይጫኑ።

ከመንግሥት ድርጅቶርች ተጠቃሚው ንክኪ ያላቸው ግለሰቦችና (የፖለቲካና የዘር) ኮንትራት ዋና ተረካቢ የሆኑ የሕወሃት ድርጅቶች (EFFORT) ናችው። በተለይ በ2012 ይህ በመሃል አገር እየጎላ መጥቷል ። የEFFORT ድርጅቶች በ 2009 እና 2010 አንዳቸውም (ከጉና በስተቀር) አትራፊ መሆን አልቻሉም ያለው ሕወሃት፣ በ 2012/2013 ትርፉ እጥፍ እንደሚሆን አሰምቷል። ለመረጃ ያህል ስለዚሁ በእንግሊዝ መንግሥት ገንዘብ የተዘጋጀውን ጽሁፍ ይመልከቱ Rethinking business and politics in Ethiopia: The role of EFFORT, the Endowment Fund for the Rehabilitation of Tigray (2011)

የእዚህ አስተሳስብ ኒዎ ሊበራሊዝም አይዲኦሎጅያዊ ምናምንቴነት ምኑ ላይ ይሆን?

ኢትዮጵያ ከፍተኛ ዕድገት ስታስመዘግብ ቆይታለች። ይህ አከራካሪ አይደለም። ይህ ዕድገት ግን ቀድሞ ባሳየው ጥንካሬ ለመቀጠሉ አጠራጣሪ ምልክቶች ይታያሉ። ዳታው ስላለው ድርጅቱም ይሀንኑ ነው የመስከረው። ይህ ደግሞ ለአገሮች አዲስ ነገር አይድለም ።አዲስ ነገር ቢኖር፡ ከዚህ በፊት በዓለም ታሪክ ታይቶ ባልታወቀ ስፋት፣ አዲስ ጥናት እንድሚያሳየው፤ ከ 2003-2007 ድረስ አዲስ ታዳጊ አግሮች (emerging economies) ዕድገት ከ3.6 % ወደ 7.2 % አድጓል። በ 2007 የ183 አገሮች ኤኮኖሚ ከ5% እና ከዚያ በላይ አድገዋል። ብዙዎቹ አገሮች አሁን በዚያ በ2007 እና ከዚያም በኋላ ያዩት ዕድገት ላይ አይደሉም (ለዚህ ይህንን ይመልከቱ Breaking Out Nations: In pursuit of the next economic miracles (Rucher Sharma, 2012)። ቻይና ብራዚል ሕንድ… እነዚህ አገሮች ሁል ተቀዛቅዘዋል። ይህ ወደ ኢትዮጵያ ቢዛመት ለምን አስገራሚ ይሆናል?
የአቶ በፈቃዱ ኢኮኖሚክስ ይህንን መናበብ ካልቻለ ከዚህ ባዶ ክርክራችው ተነስቼ የማየው ችግሩ ያለው በሳቸው አመለካከት በኩል ይመስለኛል።

በእኔ በኩል ከሁሉ የከፋ ሆኖ ያገኘሁት በእርሳቸው አመለካክት ጽሁፌ የኢትዮጵያን ሕዝብ ጥቅም አይንጸባርቅም ከማለት አልፈው፤ ወጣቱን የሚያሳስት ነው የሚለው ገለባነት ነው። በአሳብ ደረጃ ከመታግል ይልቅ እንደነ ሟቹ መለስና እንደቀሪው በረከት ስምኦን ሰው ላይ ቅጽል መለጠፍ ከጥሩ ምሁር አይጠበቅም።

አንደኛ ደግነቱ የዛሬ ወጣቶች እኛ በእነርሱ ዕድሜ ከነበርንበት ይልቅ፤ ስላሉበት ዓለም ስፋ ያለ ግንዛቤ አላችው። የኔን ጽሁፍ የሚያነቡበት ደረጃ ላይ ከሆኑ ደግሞ አንብበው ለምጠቀምም ሆን ለመጣል ችሎታው ይኖራቸዋል።

ሁለተኛ ስለ ጥሩ ኢትዮጵያዊነቴና ለአገር ተቆርቋሪነቴ የአቶ ፈቃዱ በቀለ ምስክርነት በምንም መንገድ እንደማያስፈልግኝ ቢገነዘቡልኝ ታላቅ የመንፈስ ዕርካታ ይስጠኛል።