‹‹የታላቁ ሩጫ ሀብትና ንብረት ተላልፎ ይሰጥ ቢባልም ተገቢነቱ ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ነው›› ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከተቋቋመለት ዓላማ ውጭ በንግድ ተቋምነት እየተንቀሳቀሰ ነው በሚል እስካሁን ያፈራው ሀብትና ንብረት ድርጅቱ በተቋቋመበት ዓላማ ጋር ተዛማጅነት ላለው ተላልፎ እንዲሰጥ የበጎ አድራጐት ድርጅቶችና ማኅበራት ምዝገባ ኤጀንሲ ውሳኔ ላይ ደርሷል፡፡