አዲስ መጽሐፍ ከዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል



ለሞት እንዳልተኛ ዓይኖቼን አብራ
!

መጽሐፉ ምንም እንኳን የዛሬ አንድ ዓመት ከሦስት ወራት በፊት ሙሉ ዝግጅቱ ተጠናቅቆ ወደ ማተሚያ ቤት አምርቶ የነበረ ቢሆንም በአንዳንድ ምክንያቶች የሕትመት ሂደቱ ተቋርጦ አንዲዘገይ ግድ ብለዋል። በዚህ ቆይታ መካከል መጽሐፉ በአራት የሥነ መልኮት መምህራን፣ የሥነ ጽሑፍና የህግ ባለ ሞያዎች እንዲታይና እንዲገመገም ዕድል ፈጥሯል። መጽሐፉ በይዘቱ 262 ገጽ ሲኖረው በርካታ ጥልቀት ያላቸውን ርዕሰ ጉዳዮች አንሥቶ የሚያትትና የሚያብራራ ነው። ከሞላ ጎደል በእያንዳንዱ ምዕራፍ የመጀመሪያ ገጽም የምዕራፉን አጠቃላይ ይዘት በዐጭሩ ያስቃኛል። በህትመት ረገድም በከፍተኛ ይዘትና የህትመት ጥራት በምእራቡ ዓለም የህትመት ደረጃ በላቀ ጥራት በአሜሪካን አገር ቺካጎ ከተማ በሚገኘው ትልቁ የህትመት ድርጅት የታተመ ሲሆን እስከ ድህረ ሞት ቅዱስ ፓትሪያሪክ ጳውሎስ ያለውን የማኅበሩ መሰሪ እንቅስቃሴ አካቶ በብዙ ተግዳሮትና ፈተናዎች አልፎ በዛሬው ዕለት ለንባብ መብቃቱን ይፋ ሳደርግ በታላቅ ደስታ ነው።

መጽሐፉ የማኅበሩ (ማኅበረ ቅዱሳን) ከአስመራ እስከ ደቡብ አሜሪካየዘረጋውን የልዩ ተልእኮ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ጨምሮ በዋናነት አስራ ሦስት ዓበይት ርዕሰ ጉዳዮችን አንስቶ ይዳስሳል። በተጨማሪም መጽሐፉ ከአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን፣ ከአህጉረ ስብከቶች እንዲሁም ከካህናት ጉባኤና ሊቃና ጳጳሳት “የሕግ ያለህ!” ሲሉ በማኅበረ ቅድሳን ላይ በጥብቅ የተጻፉትን ማኅበሩ የሞት ሽረት ትግል ታግሎ ከመዝግብ ቤት እንዲወጡና ደብዛቸው እንዲጠፉ ያደረጋቸው ለሰሚ ጆሮ ጭው የሚያደርጉ ልብ የሚሰብሩ የስምታና የዋይታ ደብዳቤዎች ከጸሐፊው ሰፊና የላቀ ትንተና ይዟል

ብጽእ አቡነ መልከ ጸዲቅ እኔ ለሕዝብ የማስተላልፈው መልእክት፣ ይህ በስም የተሸፈነ ማኅበር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ከሥሯ መንግሎ የሚጥላት ከባድ ጠላት መሆኑን ዐውቆ ዐወቅንብህ! የጥፋት ተልእኮህንም ዐውቀንብሃልና ከእኔ ራቅ እንዲለው ያስፈልጋል። ሊወገድ ይገባል!” ሲሉ ስመ ጥሩ የወንጌል አርበኛው አባ ወልደ ትንሳኤም የሃይማኖት ካባ ለብሶ በረቀቀ ሁኔታ የግል ጥቅሙን የሚያሳድድ: በመግደል እግዚአብሔርን አስደስታለሁ ብሎ የሚያምንበማለት በልዩ መልኩ ከመጽሐፉ አዘጋጅ ጋር ባደረጉት ቆይታ ጆሮ ያለው መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት! ሲሉ ተማጽኖዋል። የሌሎች ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን የምህጽንታ ሙሉ ቃልም በመጽሐፉ ያገኙታል:: ይህ መጽሐፍ አስቀድሞ ከፊታችን አደጋ እንዳለ ጠቋሚ በመሆን እንዲያገለግልና ክፉው ቀን እንደ ወጥመድ ሳይደርስብን ዛሬ ላይ የዳኛ ያለህ! የትድግና ያለህ! ብሎ የዜግነት ኀላፊነቱን ለመወጣት እግዚአብሔር በሰጠውመንፈሳዊ ዐደራም የራሱን ድርሻ ለማበርከት ጥረት ከሚያደርግ አንድ ኢትዮጵያዊ የተበረከተ ለኢትዮጵያና ለቤተ ክርስቲያን እድገት ሰላም፣ ለኢትዮጵያውያን አንድነት፣ ፍቅርና እኩልነት ከሚቆረቆር ሰው የተሰጠ በመሥዋዕትነት የቀረበ በረከት ነው፡፡

መንግሥትና ሕግ ባለበት ሀገር ሕጋዊ የሚያስመስል ጭንብል ለብሶ፣ ሕጋዊ እንድሆን ፈቃድ ሰጥቶኛል ለሚለው አካል እንኳ የማይገዛ፣ በሀገሪቱ ዘመናዊ ትምህርታቸውን በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚከታተሉ የአገር ተስፋ የሆኑ ዜጎችን ያለከልካይ እየመለመለ ለክፉ ዓላማው በማደራጀት ከቤተ ክርስቲያን አልፎ ለመንግሥትና ለሀገር ሥጋት የሆነ፣ በልዩ ልዩ ሕገወጥ በሆኑ መንገዶች ከሀገር ውስጥና ከውጪው ዓለም የሚሰበስበውን፣ ከፍተኛ ገንዘብ ለምን ዓላማ እያዋለው እንደሆነ፣ ለማንም ሊታወቅ ባልተፈለገ ሁኔታ፣ ተጠያቂነት በሌለበት ለ20 ዓመታት ኦዲት ሳይደረግ የሚንቀሳቀስ ተቋም በኢትዮጵያ መኖሩ ይደንቃል፡፡ ያውም በማኅበሩ ሰይጣናዊ ሥራ ስማቸው የጠፋ፣ ከአገልግሎትና ከሥራ የተፈናቀሉ፣ የተደበደቡና የተሰደዱ፣ የተደፈሩና የተገደሉ … ብዙ ንጹሐን ዜጎች የፍትሕ ያለህ!! የትድግና ያለህ!! እያሉ ከፍተኛ ጩኸት እያሰሙ አቤት የሚል የዜጎችን ሕገ መንግሥታዊ መብት የሚያስከብር መታጣቱ ይገርማል!!! እኔ ከጅምሩ መንፈሳዊ ዓላማን አንግቦ መንፈሳዊ ሆኖ ለመሥራት አስቦ እንዳልተነሣ ከቁጥር አንድ ጀምሮ በጻፍኳቸው መጻሕፎቼ ለመግለጽ ሞክሬያለሁ፡፡

በአጠቃላይ ማኅበረ ቅዱሳንተብሎ ስለሚታወቀው አገር አጥፊ ድርጅት ለሚያነሱት ማንኛውም ዓይነት ጥያቄ እንዲሁም ለማወቅ በሚሹት የማኅበሩ ስውርና ልዩ ሀገርንና ትውልድን የማተረማመስ አጀንዳ የቅድስት ቤተክርስቲያን ሰነዶች ጮኸው የትድግና ያለህ! ሲሉ ታዳጊ ፍለጋ ስምታቸውን የሚያስተጋቡቡት: አቤት! የሚሉበት መጽሐፍ ነው። ታድያ ከእርስዎ የሚጠበቀው ይህን መጽሐፍ በማንበብ የሺህ ዘመናት ታሪክ ያላትን ቤተ ክርስቲያንንና እንቢ ለባእድ! እያለች የመጣውን ሂሳቡን እየሰጠች ዛሬ ላይ የደረሰችውን ለባእድ ያልተንበረከከች ሉዓላዊት ሀገርዎት (ሀገራችን) ኢትዮጵያንም ያተርፉና ይታደጉ ዘንድ ነው

የመጽሐፉ ሽፋን ትርጓሜ:ራሱን ማኅበረ ቅዱሳንበማለት የሚጠራ ኃይማኖታዊ ካባ አጥልቆ በስመ መንፈሳዊነት ፀረ ሀገር፣ ፀረ ትውልድና ፀረ ቤተክርስቲያን ዓላማ አነግቦ ለጥፋት ታጥቆ የተነሣ ልበ ደንዳና ምግባረ እኩይ ስብስብ ሌላ ማንም ሳይሆን ማኅበረ ቅዱሳንማለት የምድሪትዋን ዘር/ፍሬ የሚበላ፣ የሚያጨናግፍና የሚያወድም አውዳሚ በላተኛና አጥፊ እሳት ነው!ሲሉ የመጽሐፉ አዘጋጅ የመጽሐፋቸው ውጫዊ ሽፋት እሳት አልብሰው አመሳጥረውታ። በዚህ አጋጣሚ ለኢትዮጵያውያን በመላ የማስተላልፈው መልእክት ቢኖር አበው “አባት ሳላ አጊጥ ጀንበር ሳለች ሩጥእንዲሉ የተረገዘው መወደለዱ አይቀርምና የዋይታ ቀን ሳይመጣ ከዚህ ከሚባላ እሳት ራሱን: ቤተክርስቲያኑንና ሀገሩን ይጠብቅ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም በሀገር ፍቅርም እጠይቃለሁ።

መጽሐፉ: ቀጥሎ በዝርዝር በሰፈሩ ከተሞች በሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት በቅርበት ያገኙታል

በአሜሪካ

ዋሽንግተን ሲያትል

ኔቫዳ – ላስቬጋስ

ካሊፎርኒያሎስ አንጀለስ፣ ኦክላንድ፣ ሳን ፍራሲስኮ

ጆርጂያ – አትላታ

ቴክሳስ ዳላስ

ኢንዲያና – ኢንዲያናአፕለስ

በአውሮፓና አከባቢዎችዋ

ኢንግላድ – ሎንዶን

በአውስትራሊያ

ሜልቦርን

በአፍሪካ

ኬንያ

ኡጋንዳ እንዲሁም ሳውዝ አፍሪካ

በኢትዮጵያ

አዲስ አበባ፣ አዋሳ፣ ናዝሬት፣ ደሴ፣ ጅማ፣ ጎንደር፣ ድሬዳዋና መቀሌ

ለጊዜው በማዕከልነት ከተዘረዘሩ ከተሞች ውጭ ለምትገኙ ወገኖች መጽሐፉን በተናጠልም ሆነ በብዛት ለማግኘት ጸሐፊው ወይንም ደግሞ የስርጭት ክፍል አስተባባሪውን በሚከተለው አድራሻ በመጻፍ ለጥያቄዎ መልስ ያገኛሉ። [email protected], [email protected]