የ40/60 ቤት ግንባታ ተመዝጋቢዎች ሥጋታቸውን እየገለጹ ነው

‹‹ቅዳሜ ምዝገባ ጀምሩ ተብለን ቀይ ልዩ የቁጠባ ደብተሮች ሰጥተውን ነበር›› የንግድ ባንክ ሠራተኞች

በታምሩ ጽጌ

መካከለኛ ገቢ ላላቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች መንግሥት ሊገነባቸው ላሰበው የ40/60 ቤቶች፣ በውስጥ ትዕዛዝ ትናንትና ምዝገባ ሊጀምርባቸው ለነበሩት 15 ሺሕ ቤቶች ለመመዝገብ የተዘጋጁ ነዋሪዎች ሥጋታቸውን እየገለጹ ነው፡፡