ፕሬዚዳንት ግርማ ሐሳብን የመግለጽ መብት በተግባር ተተርጉሟል አሉ

•    ሥልጣን የተረከበው መንግሥት በመለስ ራዕይ ላይ እንዲሠራ አሳስበዋል

በዮሐንስ አንበርብር

የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ሦስተኛ ዓመት የጋራ ስብሰባን በንግግራቸው የከፈቱት ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ፣ ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን ለማስጠበቅና ለማጠናከር የተቋቋሙ ተቋማት ባለፉት ዓመታት የተወጡትን ሚና በማድነቅ፣ በአገሪቱ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ሕጋዊ ዋስትና እንዳገኘና በተግባር እንደተተረጐመ ተናገሩ፡፡