በከፍተኛ ወጪ የተሠራው መንገድ ለባቡር ግንባታ መፍረሱ አነጋጋሪ ሆኗል

በውድነህ ዘነበ

በከፍተኛ ወጪ ተገንብቶ በቅርቡ ለትራፊክ ክፍት የተደረገው የቃሊቲ መስቀል አደባባይ የአስፓልት መንገድ መካከኛው ክፍሉ ለባቡር ሐዲድ ግንባታ ሲባል እየፈረሰ ነው፡፡ የአስፓልቱ መፍረስ በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ መነጋገሪያ ሆኗል፡፡