ንግድ ባንክ ያለ በቂ ዋስትናና የሒሳብ ሰነድ ከፍተኛ ብድሮች መፍቀዱን ሰነዶች አረጋገጡ
በጋዜጣው ሪፖርተር
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያወጣውን የብድር ፖሊሲና የተቆጣጣሪውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፖሊሲዎች በመጣስ፣ ከፍተኛ የዕዳ ጫና ላለባቸውና ከሰባት ዓመት በላይ ኪሳራ ሲያስመዘግቡ ለቆዩ ተበዳሪዎች፣ የባንኩ ፕሬዚዳንት ከተሰጣቸው ሥልጣን ውጪ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ብድሮች እንደፈቀዱ ለሪፖርተር ጋዜጣ የተላኩ ሰነዶች አረጋገጡ፡፡