ራዕይ አልባው ወራሽ!
(ታላቅሰው ምንአለ ከአ.አበባ)
በኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም ዘመን ትምህርታቸውን ተከታትለው በማዕርግ መመረቅ ከቻሉ የዐመድ አፋሿ እናት ሃገር ልጆች መካከል አንደኛው ነበር። ጥሎበት የመረጠውንና የዕለት እንጀራዬን ያሳምርልኛል ያለውን ሙያ ብቻ መከታተልን እንጂ ፖለቲካ ይሉትን ነገር እነደኮረንቲ ሲሸሽ ነው የኖረው። ጨዋነት ተፈጥሮው ነው። “እሺ” ባይነት መለያ ባሕርይው።