ርዕሰ-አድባራት ደብረ-ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተ-ክርስቲያን፣ 25ኛ የብር ኢዮቤልዮ በዐል፣ በዋሽንግተን ዲሲ
መሥራቾቿ እነ መጋቤ-ካህናት ከሀሊ ወንዳፈረው የዛሬ ፳፭ ዓመት፣ ደብረ-ሰላም ቅድስት-ማርያም ብለው ያቋቋሟት ይህች ቤተ-ክርስቲያን፣ በኋላ ነው፣ ሰፊ አገልግሎቷንና ቀዳማዊነቷን የተገነዘቡ ሁለት ብጹአን ሊቃነ-ጳጳሳት፣ አቡነ ይስሐቅና አቡነ ዜና-ማርቆስ በሕይወት በነበሩ ጊዜ «ርዕሰ-አድባራት» ብለው የሰየሟት።
በብዙ ሺህ የሚቆጠሩት ህፃናትን እያጠመቀች፣ የብዙ መቶ ወጣቶችን የጋብቻ በዐል በሥርዓተ-ተክሊል እየፈጸመች፣ ከዚህ ዓለም ለተለዩ አያሌ መቶዎች ፍትሐተ-ጸሎት እያደረሰ፤ ቀሪ ሕይወታቸውን በንጽሕና ለማሳለፍ ለወሰኑ ለብዙ ምዕመናንና ምእመናት የምንኩስና ማዕርግ እየሰጠች፣ ታዳጊ ወጣቶችን የሃይማኖት ትምህርትና የኢትዮጵያን ባህልከነ-ፊደሏ እያስተማረች፣ ጠቅላላ ምእመናኗን በቅዳሴና በጸሎት እያገለገለች እነሆ ለ፳፭ ዓመታት ተጉዛ እዚህ ደርሳለች።
ዋና …