የነፃነት ዘይቤ
ሰሎሞን ተሠማ ጂ.
“ነፃ-አውጪ” ነን ባዮችና “የነፃነት ታጋዮች/ተጋዳላዬች” ናቸው የሚባሉት ወገኖች ቁጥር ቀላል አይደለም። ለአብነት ያህል እንኳን “ሕወሐት- ሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ” (ወያኔ)፣ “ሕሐኤ- ሕዝባዊ ሐርነት ኤርትራ” (ሻዕቢያ)፣ “ኦነግ- የኦሮሞ ነፃነት ግንባር”፣ “ኦብነግ- የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር”፣ “ግ7ፍነን- የግንቦት 7፣ ለፍትሕና ለነፃነት ንቅናቄ”፣ “እኦነግ- የእስላማዊ ኦሮሚያ ነፃነት ግንባር (ጃራ)”፣ “አሕነግ- የአማራ ሕዝብ ነፃነት ግንባር” እና ከቅርብ ጊዜ ወዲህም “ነኢጦ- ነፃ የኢትዮጵያዊያን ጦር” የሚባል እንቅስቃሴም ስለመኖሩም ተሰምቷል። ከወያኔ በስተቀር፣ ብዙዎቹ “በሽብርተኝነት” የተፈረጁ ድርጅቶች ናቸው።