ሚድሮክ የብረታ ብረት ፋብሪካ ለማስገንባት የ764 ሚሊዮን ዶላር ውል ሊፈራረም ነው

በውድነህ ዘነበ

የሚድሮክ ሊቀመንበር ሼክ መሐመድ አል አሙዲ ጦሳ የተሰኘውን የብረታ ብረት ፋብሪካ እንዲገነባላቸው ከተመረጠው የጣሊያን ኩባንያ ጋር 764 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ የግንባታ ውል የፊታችን ማክሰኞ ይፈራረማሉ፡፡