ዊኪሊክስ በኢትዮጵያ አውሮፕላን ላይ ተፈጽሟል የተባለውን ሴራ አጋለጠ

–    ኢትዮጵያውያን የሂዝቦላ መረጃ አቀባዮች የቤት ሠራተኛ ተመስለው አታለዋል

በአስራት ሥዩም

በዓለም እጅግ አነጋጋሪና ገናና ለመሆን የበቃው የዊኪሊክስ ድረ ገጽ ይፋ ባወጣው አዲስ መረጃ የበረራ ቁጥር “ET-409” የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 አውሮፕላን፣ ከቤይሩት ራፊቅ ሐሪሪ አውሮፕላን ማረፊያ ጥር 17 ቀን 2002 ዓ.ም. ከመነሳቱ ወዲያው ሲከሰከስ፣ የእስራኤል የስለላ ድርጅት ሞሳድ በተሳተፈበት ምስጢራዊ የደኅንነት ሥራ ሳቢያ ሰለባ ሳይሆን እንዳልቀረ አመለከተ፡፡