ፀረ-ማርያም ፖለቲካ
ተስፋዬ ገብረአብ
ስብሃት ነጋ፣ በፓልቶክ ክፍል ተጋብዞ ባደረገው ንግግር፣ “ለኦርቶዶክስ ወይም ለአማራ ብቻ ተወስኖ የቆውን የኢትዮጵያ መንገስታዊ ስልጣን ለተጨቆነው ህዝብ አስረከብነው” ማለቱን አንድ ጓደኛዬ ነገረኝ። ይህን የነገረኝ ጓደኛዬ በስብሃት ንግግር በጣም ተገርሞ ስለነበር፣ “አታስብ! ስብሃት አብሻቂ የንግግር ጠባይ አለው።” ስል ጠቆምኩት። ለነገሩ በሚናገረው ባልስማማም፣ ስብሃት ያመነበትን እንደወረደ ስለሚያፈርጠው ከሌሎቹ እሱ ይሻለኛል። “በዚህች አለም ላይ መጥፎም ይሁን ጥሩ ያመንክበትን ፈፅመህና የልብህን ተናግረህ ማረፍን የመሰለ እርካታ የለም” ይል ነበር መለስ ዜናዊ – ነፍሱን ይማረውና።