የንግድ ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት በሙስና ተጠርጥረው ታሰሩ
በጋዜጣው ሪፖርተር
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሰው ሀብት አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንት የሆኑትና ባለፈው ዓመት የንብረትና ግዥ አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ሰይፉ ቦጋለ፣ ከመንግሥት ደንብና መመርያ ውጪ በቀጥታ ከአንድ የግል ድርጅት ጋር ፈጽመው ነበር በተባለው ከ12.9 ሚሊዮን ብር በላይ ሕገወጥ የኮምፒዩተር ግዥ ተጠርጥረው፣ በሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አማካይነት ካለፈው ዓርብ ጀምሮ በቁጥጥር ሥር እንደሚገኙ ተገለጸ፡፡