የህንዱ ኩባንያ በብረት ማዕድን ፍለጋ ላይ አነጣጥሯል
• በዓመት 60 ሺሕ ቶን ቆርቆሮ ማምረት ይጀምራል
በብርሃኑ ፈቃደ
ከሁለት ዓመት በላይ የፈጀው የግንባታ ሥራ በከፊል ተጠናቅቆ በቆርቆሮ ምርት ወራትን ያስቆጠረው አርቲ ስቲል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ፣ ባለፈው ቅዳሜ የጋልቫናይዝድ ቆርቆሮ ማምረቻውን ባስመረቀበት ወቅት ለማወቅ እንደተቻለው በብረት ማዕድን ፍለጋ ላይ ማነጣጠሩን ነው፡፡