ስለጠ/ሚ/ር ኃይለማርያም ደሳለኝ ያልተባሉና ያልተነገሩ ነገሮች በቀድሞ ተማሪያቸው ዕይታ

ከአቶ ኃይለማርያም የቀድሞ የዩነቨርሲቲ ተማሪ
I. መግቢያ፡-
የጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊ ድንገተኛ ሞት ተከትሎ የአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ያልተጠበቀና ያልታሰበ ወደስልጣን መምጣት ብዙዎችን ያስገረመ ጉዳይ ሲሆን ይህንንም ተከትሎ የዚች ሃገር ጉዳይ ያገባኛል ያሉ ብዙ ግለሰቦች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማሀበራት እና ሌሎችም የሳቸው ሹመት ለሃገሪቱ ጥሩ አጋጣሚ ሊሆን እንደሚችልና ምናልባትም ፈጣሪ ለዚች ሃገር ለውጥ ያስቀመጣቸው ሊሆኑ ሁሉ እንደሚችሉ ተስፋ አድርገውባቸዋል። እኔም ከነዚህ ወገኖች አንዱ ነኝ።